by NoViolet Bulawayo
translated by (T)Sedey Gebreyes

በኖቫዮሌት ቡላዋዩ
ትርጉም በፀደይ ገብረየስ

ጥሪ ለድንበር አቁአራጮች ቤታቸውን ላጡ የሃዘን ተራማጆች። ጥሪ ለጥቁሩ ወገኔ የልቡ ትርታ በፖሊስ ጥይት ለተቀማበት።
ጥሪ ለእስረኛ እናቶች የጡት ወተታቸው ታፍኖ ለረጋባቸው።
ጥሪ ለተረሱ ሰውነቶች የመካከለኛውን ባህር የሃዘን ውሃ ተጋቾች። ጥሪ ለሃገር የለሽ ነዋሪ ከቀዬው ለተፈናቀለው።

ጥሪ ለአርሶ አደሩ ሳንባው በተባይ አጥፊ ለሳሳበት።
ጥሪ ለባእዳን፥
ጥሪ በወደቁ የትምህርት ቤቶች ለእስረኛነት ለሚሞሸሩ ህፃናት።
ጥሪ የእስርቤትን ጉሮሮ ላጨናነቁ ወንድሞች፥ አባቶች እና አጎቶች።
ጥሪ እግሮቻችው ለዛሉባቸው ዘበኞች፥የቤት ሰራተኞች፥እንዲሁም ሞግዚቶች። ጥሪ የመኖሪያ ወረቀት ለሌላቸው።
ጥሪ ለተጨቆኑ እና በከንቱ ፍትህን ለሚጠብቁ።
ጥሪ ለስም የለሽ ወገኖች በፆታቸው ምክንያት ለሚገደሉ።
ጥሪ ሃገር ለሌላቸው ዜጎች።
ጥሪ በድንበር አስከባሪዎች ለፈሰሰው ደማቁ የስደተኞች ደም።
ጥሪ ስለማደሪያው ስለሚያልመው የጎዳና ተዳዳሪ።
ጥሪ በገዛ ላቡ ወንዝ ውስጥ ለተጠመቀው ወዝ አደር።
ጥሪ ለተገፉ እና ለተረሱ።
ጥሪ ለእርዳታ ምግብ ለተሰለፉ እናቶች።
ጥሪ ለስደተኛ ወላጆች ልባቸው እየደማ ልጆቻቸውን ለተከፋፈሉ።
ጥሪ እስኪሸኙ ለሚጠብቁ ጥገኞች።
ጥሪ ታፍነው ዛሬ ነገ ለሚሉ ለጥቁር ወገኖቼ።
ጥሪ ለደሃው ዎገኔ ቀን እስኪዎጣለት ለሚጠብቀው።

ጥሪው በእያንዳንዳችን ስም የፀደቀ አላማ እና ስለየአንዳንዳችን የተፀለየ ፀሎት ነው።
ጥሪው የሚያድነን ዜማ ነው።
ጥሪው የበለዘውን ስብእናችንን የሚፈውስ ዘይት ነው።
ጥሪው ልቦናችንን አጢነን እንድንመለከት የሚያደፋፍረን የእውነት መስታዎት ነው።
ጥሪው ቀድሞውንም ከተፈጥሮ ውጪ እና ሰው ሰራሽ ከሆኑት ድንበሮች በላይ የተገነባ ድልድይ ነው። ጥሪው ስንፋለመው የኖርነውን ጨለማን ውጦ በፍትህ ብርሃን እንድንቀመጥ ያደረገን መብራት ነው። ጥሪው በፖሊስ እና በድንበር አስከባሪዎች ለተረሸኑ ወገናት የተገጠመ የሃዘን እንጉርጉሮ ነው።

ጥሪው በነፃነት እና በፍቅር ወደምንድኖርበት አለም የሚያመራ የእጣ ፈንታችን ካርታ ነው።
ጥሪው ዝምተኝነትን የሚፃረር ከባንግላዴሽ እስከ ባልትሞር ፥ በፈርገሰንም፥ በጆሃንስበርግም ፥ በሜክሲኮም ዙሪያ፥ በኤልሳለቫዶር እና በአሜሪካ ዙሪያ ሁሉ የሚሰማ ድንበር የሌሽ ደውል ነው።
በፎልሰምም የክፍለ ከተማ ከርቸሌ እንዲሁ ፤ በየመንገዱም ሁሉ። ከሲሪያ እስከኮሶቮ። በቻይናም በኤርትራም። በካንቦዲያም እንዲሁም በሄቲ። በክሬን ካውንቲ ቴክሳስም። በፍተሻም ቦታ ሆነ በቤት ጟሮ።

ጥሪያችን በሁሉም ቋንቋዎች ነው።
ከሻከረ ጉሮሮአችን የሚወጣው ድምፅ ዐለምን እስኪያንቀጠቅጥ እና እስኪደመጥ ድርሰ አያቆምም። እየታፈኑ እና እይተበደሉ ያሉ ስሞች ዜማ እስኪከበር ድረስ፥ የሁላችንም ስሞች እስኪከበሩ ድረስ። ስብእናችን ላይ የታወጀው ጦርነት እስከያቆም ድረስ የትም አንሄድም።

ሰንሰለቶች እስኪሰበሩ ድረስ ከአጥናፍ እስከአጥናፍ ተያይዘን እንቆማለን።
ከዚያም አጥሮች ያፍርሳሉ።
ከዚያም ሊከፋፍሉን ያሰመሩአቸውን መስመሮች ያጠፋሉ ድንበሮችንም ይከፍታሉ። ከዚያም ጣሪያዎችን ያፈርሳሉ።
ከዚያም ፍትህ በየቀያችን ይደርሳል።
ከዚያም የመኖር ዋስትናችን በአለም ይከበራል።

ምክንያቱም ሁላችንም ነፃ እስክንዎጣ ድረስ አንቺ ንፃ አደለሽም ።
ጩኸታችን አለምን አስተካክለን የመኖሪያ ቦታ እስክናስመስለው ድረስ ጥሪያችንን አናቆምም፥ ለሌሎችም ጥሪ እናቀርባለን። ከሩቅም ከቅርብም ከእላም እና ከእታም ያሉትን እንጣራለን። ከቤትም ከስደትም ቦታ ሆነን እንጮሃለን። በሮችን እያን

ምክንያቱም የቆዳችንን ቀለም እንደ ጌጥ ለብሰን በሮች ሳይዘጉብን መመላለስ እንሻለን። ማንነታችን ሳይመረመር፥ይህም በትምህርት ቤትም ሆነ በስራ ቦታ፥ በሰላማዊ መኖሪያዎችም ሆነ በተሻለ መስተንግዶ እና የስራ እድል ይታያል በውይይቶችም ቦታ እንዲሁ።
ከእኛ በፊት የነበሩ ወገኖቻችን ለነፃነታችን ሲሉ የተጋደሉባቸውና ህይወታቸውን የሰውባቸው ቦታዎችም ላይ ይታያል።

ለአለም እንደ አይን ብርሃን የሆኑትን ንፁሃን ጥቁር ህፃናትን እንጠራለን። የተባረኩ ናቸውና የፖሊስ አፈሙዝ ሳያዩ እና ሳይገደሉ በሰላም ያድጋሉ ይጎለብታሉም። አሸናፊዎች ናቸው ምክንያቱም ይመገባሉ መጠለያ ይኖራቸዋል ህክምናን ያገኛሉ ትምህርትም እድልም ፍቅርም ውበትም ከፀሃይ በታች እንደልባቸው የእነሱ ናችው። ምክንያቱም ወላጆቻቸው እስርቤት ሳይሆን እቤታቸው ሆነው ያሳድጉአቸዋል። ምክንያቱም የሚኖሩባት አለም ስለ እንሱ የምትዋጋ እንጂ እነሱን የምትወጋ አይደለችም።

ምክንያቱም ጭቆና እዚህ ላይ ያቆማል።
ምክንያቱም የሰው ልጅ ክብር አሁን ይጀምራል።
ማስተዋል ያላቸውን ሃገራትን እንጠራለን። ለእነሱ ሲሉ የደሙላቸውን ያበሉአቸውን የጠበቋቸውን የያዙዋቸውን አጆች እና የተራመዱላቸውን እግሮች የሚስሙ። የሰጡአቸውን መልሰው ለሚሰጡ ምስጋናን ቋንቋ ለሚያውቁ ሃገራት ጥሪ እናቀርባለን።

ከመከራ ከበዛባቸው የስራ ቦታዎች አውጥተው የሚመሩን ሀገራትን እንጠራለን። የዛሉትን እግሮቻችንን የምናሳርፍበትን መሬት ከምስጋና ጋር ለሚሰጡን ሃገራት ጥሪ እናቀርባለን። እዛም መሬት ላይ ፖሊሶች እና ድንበር አስከባሪዎች ዳቦ እና መጠለያ ያቀርቡልናል። ለማይዘልፉንን እና ሰበአዊ መብታችንን ለሚያከብሩልንን ያጣነውን እና የሰዋነውን ለሚቆጥሩልን በእኛ ትከሻ ላይ እንደተገነቡ ለሚያውቁት ሃገራት ጥሪ እናቀርባለን።

ምክንያቱም ሰውን ሰው የሚያደርገው የሌላ ሰው መኖር ነው።

“ከየት መጣሽ? ሂጅ ከእዚ እና ወደመጣሽበት ተመለሺ።” የማይሉ ድንበሮችን እንጠራለን። መብራት አብርተው በስማችን የሚጠሩንን። በልባቸው የሚያዩንን እና ሞታችንን ለማይመኙ ሃገራት ጥሪ እናቀርባለን። ከወጀብ አውጥተው ለቁስሎቻችን መድሃኒትን ይዘው የሚጠብቁንን ሃገራት እንጠራለን።

ውበታችንን ተፈላጊነታችንን እና ክብራችንን በየማለዳው እራሳቸውን እያስታውሱ እንዳይጎዱን የሚጠነቀቁ። ይህ ደግሞ እኩልነትን የሚደግፉን ልቦች ወደ እኛ አላማ እንዲያዘነብሉ ያድርጋቸዋል። እንደ ድል ሰንደቅም ያንሱናል ውደ እውነተኛም

ኳኳን እንጮሃለን፥ተሰልፈንም እንጮሃለን። ወገኖቻችን እንደ አደን በሚያድኑአቸው ፖሊሶችና ድንበር

አስከባሪዎች እጆች ሳይነኩ በነፃነት እንዲኖሩ እንሻለን።

ፍትህ ያበሩናል። ምክንያቱም እዚህ ነን እና የትም አንሄድም እና። ነፃ እስክንወጣ ደረስ እንጣራለን፥ እንጣራለን፥ እንጣራለን። ምክንያቱም ከዚህ ኑሮ የተሻለ ኑሮ እንዳለ ተረድተናልና። ምክንያቱም ከዚህ የተሻለ ኑሮ አለና።